እስራኤል
From Wikipedia, the free encyclopedia
እስራኤል (ዕብራይስጥ፦ ישראל) በእስያ ውስጥ የሚገኝ አገር ናት። ዋና ከተማዋም አሁን እየሩሳሌም ሲባል፣ ይህንን ግን ብዙዎቹ አገራት ስለማይቀበሉ ኤምባሲዎቻቸው በቴል አቪቭ ነው የሚቀመጡ። ከዚያም በላይ 31 የተመድ አባላት ለእስራኤል ምንም ተቀባይነት አይሰጡም። በ2017 እ.ኤ.አ. (2009-2010 ዓም) ሩስያ፣ አሜሪካና ጓቴማላ ለምዕራብ ኢየሩሳሌም የእስራኤል ዋና ከተማ እንዲሆን ዕውቅና ሰጡ። አንዳንድ አገራት ደግሞ ለምሥራቅ ኢየሩሳሌም የፍልስጤም ግዛት ዋና ከተማ እንዲሆን ዕውቅና ሰጡ።
እስራኤል አገር |
||||||
---|---|---|---|---|---|---|
|
||||||
ብሔራዊ መዝሙር: הַתִּקְוָה |
||||||
ዋና ከተማ | እየሩሳሌም | |||||
ብሔራዊ ቋንቋዎች | ዕብራይስጥ ዓረብኛ |
|||||
መንግሥት ፕሬዝዳንት ጠቅላይ ሚኒስትር |
ፓርለሜንታዊ ሪፐብሊክ ረውቨን ሪቭሊን ቢንያሚን ነተንያሁ |
|||||
የመሬት ስፋት አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.) ውሀ (%) |
20,770 (149ኛ) 2.1 |
|||||
የሕዝብ ብዛት የ2017 እ.ኤ.አ. ግምት |
8,691,600 (97ኛ) |
|||||
ገንዘብ | ስሀከል (₪) | |||||
የሰዓት ክልል | UTC +2 | |||||
የስልክ መግቢያ | 972 | |||||
ከፍተኛ ደረጃ ከባቢ | .il |
የመጀመሪያ ሰዎች ከአፍሪካ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ እንደ ወጡ ይታመናል። በመካከለኛው የነሃስ ዘመን ከንዓናዊ እንደኖሩና የይሁዳና እስራኤል ግዛት በብረት ዘመን እንዳሉም የቅሪት ተመራማሪዎች አስረድተዋል። አዲሱ የአሱራውያን ግዛት እስራኤልን በ720 ዓዓ አጥፍቶ እስራኤል የመገነጠል አደጋ ደርሶባት ነበር። ይሁዳ የባቢሎኒያን፣ የፋርስና የግሪክ ተከታታይ ግዛቶች ገዝቶ ነበር። የመቃብያን አመፅን ተከትሎ የሃስሞንያ ግዛት በ110 ዓዓ ተመስርቷል። ይህም ግዛት ከሮማ ግዛት በ63 ዓዓ ጋር ሲዋሀድ፣ በ37 ዓዓ ደግሞም የሄሮድ ስርወ መንግስት ማቋቋም ጀመረ። ነገር ግን በ6 ዓዓ የይሁዳ ግዛት የሮማ አውራጃ አካል ሆኖ ነበር።
በወቅቱ የነበረውን እርስ በርስ ሽኩቻ ተከትሎ እስራኤል በ70 ዓመተ ክርስትና መፍረስ ጀመረች። አይሁዳውያን መበተን ሲጀምሩ ግዛታቸው ከይሁዳ ወደ የሶርያ ፍልስጤም የሚል ስያሜ ተሰጠው። በ7ተኛው ክፍል ዘመን እስራኤል በአረብ እጅ ቁጥጥር ስር ዋለች። ይህም እስከ 1099 ዓም በነበረው የመጀመሪያው መስቀል ጦርነት ድረስ ነበር። ከ13ተኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ የግብፁ ማምሉክ ሱልጣኔት ሌቫንትን ሲቆጣጠር ኦቶማኖች በ1517 ዓም አሸንፈው ተቆጣጠሩ። ከዛም ግዜ ጀምሮ አምባገነናዊው የፅዮን ንቅናቄ እስራኤላውያን ማከናወን ጀመሩ። ይህም ንቅናቄ እስራኤላውያን ወደ ታሪካዊ ቦታቸው እንዲመለሱ ሳይሆን በአይሁድ የሚመራ አምባገነናዊ የአለም መንግስት መመስረት ነበረ። አንደኛውን የአለም ጦርነት ተከትሎ፣ የእንግሊዝ ግዛት የሌቫንትን አጠቃላይ ቦታ ቅኝ ገዛች። የተባበሩት መንግስታት በ1947 ዓም ይህንን ግዛት ከፍልስጤም ቢያስለቅቅና፣ የእስራኤልና የአረብ ነፃ ድንበር ቢሰጥም፣ የአረብ መሪዎች ይህንን ስምምነት አልተቀበሉትም። ምንም እንኳን አጭር ጦርነት ቢያረጉም፣ እስራኤል በ1948 ዓም እንደ ነፃ ሀገር መሆን ጀመረች፣ የተወሰኑት የቀድሞ ቦታዎቿን ብታስመልስም ዌስት ባንክና ጋዛ ለግብፅና ለዮርዳኖስ ተተወ። እስራኤል ይህንን ግዛት ለማስመለስ ከአረብ ሀገራት ጋር ብዙ ግጭቶችን ብታረግም በኋላ ከግብፅና ከዮርዳኖስ ጋር ጥሩ ያለሰለሰ ግንኙነት ጀመሩ።
የእስራኤል "ቤዚክስ ሎው" (መሰረታዊ ህግ) የሚደነግገው አይሁዶች እስራኤልን እንደሚመሯትና ሉዐላዊ ሀገር እንደሆነች ነው።
እስራኤል ከሌቫንት ሀያላን ሀገር ናት። በውትድርና፣ በፖለቲካ ስርአት፣ በሳይንስና ቴክኖሎጂ እንዲሁም በጤና ዘርፍ የበለፀገች ናት። ቴል አቪቭ የእስራኤል ዋና የንግድ ማዕከል ሲሆን ብዙ አይሁዶች ያለበት ከተማ ነው። በተጨማሪም የኤልጂቢቲ መብት በእስራኤል ውስጥ በይፋ የሚንቀሳቀስበት ነው። እስራኤላውያን በጥንት ጊዜ ሲበታተኑ ወደ ተለያዩ የአለም ክፍል ተቀላቅለዋል። በዚያ የተነሣ ከአሕዛብ ጋራ በመጠኑ ተቀላቅለዋል። ቢኾንም ብዙዎቹ በይሁዲዎች በአውሮፓ በስደት እንደ መኖራቸው የይሁዲዎች መጠን በአብዛኛው የሚያደላው ለአውሮፓ ነው። በአውሮፓአህጉር የተበተኑት አይሁድም "የአሽኬናዚ ይሁዲዎች" ይባላሉ።