ሉል
From Wikipedia, the free encyclopedia
በሂሳብ ጥናት ሉል ማለት ዙሪያው በትክክል ክብ የሆነ 3ቅጥ ያለው የጂዖሜትሪ ፍጥረት ነው። በሌላ አተረጓጎም ሂሳባዊ ሉል በኅዋ ላይ ተንጣለው ያሉ ከአንድ መካከለኛ ነጥብ በእኩል ርቀት የሚገኙ ነጥቦች ስብስብ ነው። ይህ እኩል እርቀት የሉሉ ራዲየስ ሲባል ሉሉን ሰንጥቀው ከሚያልፉት ቀጥተኛ መስመሮች ሁሉ ረጅም የሆነው የሉሉ ወገብ ግማሽ ነው። በሌላ ሶስተኛ አተርጓጎም ሂሳባዊ ሉል አንድን ክብ በራሱ ወገብ ስናሽከረክረው የምንፈጥረው ሶስት ቅጥ ያለው ነገር ነው።