ጥቅምት ፳፯
- ፲፰፻፯ ዓ.ም. -ሳክሶፎን የሙዚቃ መሣሪያ የፈጠረው የቤልጅግ ዜጋ አንቶን ጆሴፍ አዶልፍ ሳክስ በዚህ ዕለት ተወለደ።
- ፲፰፻፹፮ ዓ.ም. - የክላሲክ ሙዚቃ ፈጣሪና አቀናባሪ የሩሲያው ዜጋ ፒተር ኢልዪች ቻይኮቭስኪ በፔትሮግራድ ከተማ አረፈ።
- ፲፱፻፵፱ ዓ.ም. - የግብጽ ፕሬዚደንት ጋማል አብደል ናሰር በወቅቱ በብሪታንያ እና በፈረንሳይ ቁጥጥር ስር የነበረውን የሱዌዝ ቦይ የግብጽ ብሔራዊ ንብረት ሲያደርገው የብሪታንያና የፈረንሳይ ሰራዊቶች በቦዩ አካባቢ ግዛቶች ከግብጽ ሰራዊት ጋር ተዋጉ።
- ፲፱፻፶፫ ዓ/ም - “ሚቸል ኮትስ” (Mitchell Cotts) የተባለው የብሪታንያ ኩባንያ ዋና ሥራ አስኪያጅ ከኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት ጋር በአዋሽ ሸለቆ የተንዳሆን የጥጥ እርሻ ልማት የስምምነት ውል ለመፈራረም አዲስ አበባ ገቡ።
- ፲፱፻፷፬ ዓ.ም. - አምቺትካ ደሴት ላይ የአሜሪካ የአቶሚክ ኃይል ድርጅት በምድር ውስጥ “ካኒኪን” በሚል ቅጽል ስም የተሰየመውን ኃይለኛ የሃይድሮጅን ቦምብ በማፈንዳት ፈተሸ።
- ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - አዲሱ የኢትዮጵያ ጊዜያዊ ወታደራዊ መንግሥት (ደርግ) አቶ አሀዱ ሳቡሬን የሐረርጌ ግዛት አስተዳዳሪ አድርጎ ሾመ።