ጥቅምት ፮
- ፲፯፻፹፮ ዓ/ም - በፈረንሳይ አብዮት የ ንጉሡ የሉዊ ፲፮ኛ ሚስት ንግሥት ማሪ አንቷኔት አንገቷን በመቆረጥ ተሰዋች።
- ፲፰፻፸፱ ዓ/ም - የእስራኤል የመጀመሪያው ጠቅላይ ሚኒስቴር እንዲሁም የመከላከያ ሚኒስቴር በመሆን ያገለገሉት ዴቪድ ግሪን ወይም ዴቪድ ቤንጎርዮን ተወለዱ።
- ፲፱፻፷፫ ዓ/ም - በጋማል አብደል ናስር ሞት ምክንያት በግብጽ አንዋር ሳዳት የአገሪቱ ፫ኛ ፕሬዚዳንት ሆኑ።
- ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - የዋቢ ሸበሌ ሆቴል ድርጅት በደርግ መንግሥት ተወረሰ።
- ፲፱፻፸፯ ዓ/ም - በአንግሊካን ቤተ ክርስቲያን የኬፕ ታውን ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ደቡብ አፍሪቃዊው ዴዝሞንድ ቱቱ የ ኖቤል ሰላማዊ ሽልማት ተቀባይነታቸው ይፋ ተደረገ።
- ፲፱፻፸፬ ዓ/ም - ስመ ጥሩው የእስራኤል ጄኔራል፤ እንዲሁም በአገሪቱ የመከላከያ ሚንስቴርነት እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርነት ማዕረግ የበቁት ሞሼ ዳያን በተወለዱ በ፶፮ ዓመታቸው በሞት ተለዩ።