ዒዛና
የኢዛና ውልደት እና አስተዳደግ / From Wikipedia, the free encyclopedia
ዒዛና (በግሪክ ፡ ኤይዛናስ) ፣ (ወደ ፬ኛው ክ/ዘ አጋማሽ ዓ.ም.) ፣ ከአክሱም ነገስታት ሁሉ ገናና የሆነ የመጀመሪያው ክርስትያን ንጉሥ ነበር ። ምናልባት ለአባቱ ለንጉሥ ኢላ-አሚዳ ፡ የበኩር ልጁ ሳይሆን አይቀርም ። ስለ እናቱ ሥም የሚናገር ታዓማኒ የጽሑፍ መረጃ እስካሁን ድረስ አልተገኘም ። ከሁለተኛ ደረጃ ምንጮች መሠረት ግን የእናቱ ሥም ሶፍያ ይባላል ።
Quick Facts ንጉሥ ዒዛና, የአክሱም ንጉሥ ...
ንጉሥ ዒዛና | |
---|---|
የአክሱም ንጉሥ | |
የሚቀድመው | አላ አሚዳ(አባቱ) |
የሚከተሉት | አብርሃወ አፅበሐ (ልጆቹ) |
የኢትዮጵያ ነገሥታት | |
Close
ሁለቱ ወንድሞቹ ሣይዛና እና ኃደፋ በአስተዳደር እና በውትድርና ሥራዎች ይረዱት ነበር ። በተለያዩ ጊዜያት ባደረጋቸው ተከታታይ የግዛት ማስፋፍያ ዘመቻዎች ፡ ንጉሥ ዒዛና ግዛቱን በስሜን ቤጃዎች፣ ካሡና ኖባ በተባሉ የተከዘ ቀበሌዎች ፣ በአትባራ እና በአባይ ወንዞች ፣ በምስራቅ በኩል በአግወዛት ፣ በደቡብ ስራኔ በተባለ የአፋን ምድሮች ላይ ወረራ እንደፈጸመ በግዕዝ ፣ በጥንታዊ ዐረብኛ ፣ እና በግሪክ ተጽፈው በአክሱም የተገኙ የጽሑፍ መረጃዎች ያመለክታሉ ። የግዛት ማስፋፍያ ዘመቻዎቹ ቅደም ተከተል ግን እስካሁን አከራካሪ ናቸው ።