የዮሐንስ ወንጌል
ክርስቶስ የሚወደው ከሁሉ ታናሽ ሐዋርያ የጻፈው ወንጌል / From Wikipedia, the free encyclopedia
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ቅዱስ ዮሐንስ እንደ ጻፈው። ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ይወደው የነበረው የዘብዴዎስ ልጅ ዮሐንስ በፍልስጤም ከፍልስጤምም ውጪ ክርስትና እንድትስፋፋ ያደረገ ጌታ በመስቀል ላይ ሳለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን እንዲያገለግላት አደራ የተቀበለ የእመቤታችን የአደራ ልጅ ነው (ዮሐ. ፲፱፡፳፮)።
Quick Facts ቅ.ዮሐንስ ወንጌላዊው, ክርስቶስ የሚወደው ደቀመዝሙር የሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌል ...
ቅ.ዮሐንስ ወንጌላዊው | |
---|---|
ክርስቶስ የሚወደው ደቀመዝሙር የሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌል | |
የፀሐፊው ስም | ዮሐንስ |
የተወለደበት ቀን | በ፩ኛው ክፍለ ዘመን በ፲ኛው ዓመት |
የተወለደበት ቦታ | ቤተሳይዳ |
ሥራው | ወንጌል ሰባኪ ፀሐፊም |
ያረፈበት ቀን |
ሞትን አልቀመሰም (ተነጥቋል) |
ንግሥ | ጥር ፬ |
መታወቂያው | |
የሚከበረው | በመላው የክርስትና እምነት ተከታይ |
የጻፈው ወንጌል | ፳፩ ምዕራፍ |
በተጨማሪ የፃፋቸው |
የዮሐንስ ራእይ ታዐምረ ኢየሱስ |
← የሉቃ.ወንጌ የሐዊ.ሥራ፩ → |
Close
ከዚህም ጋር ከቅዱስ ጳውሎስ ዕረፍት በኋላ ከኢየሩሳሌም ወደ ኤፌሶን ሄዶ በትንሽዋ እሲያ ወንጌልን የሰበከ በሮማዊው ቄሣር በዶሚቲያኖስ ዘመነ መንግሥት ወደ ፍጥሞ ደሴት ተሰዶ በእስር ቤት ሳለ ራእይን የጻፈ ነው ።
Quick Facts
Close
ከዶሚቴያኖስም ሞት በኋላ ወደ ኤፌሶን ተመልሶ " ልጆቼ እርስበርሳቹህ ተፋቀሩ " እያለ ያስተማረ በስሙ የሚጠሩትን ወንጌልን እና ሦስቱን መልዕክታት የጻፈ ንባቤ መለኮት የሚል ስያሜ የተሰጠው ሐዋርያ ነው። ወንጌሉም ጌታ ከዐረገ በኋላ በሠላሳ ወይም በሠላሳ አምስት ዓመት ኔሮን ቄሣር በነገሠ በስምንት ዓመት በየናኒ ቋንቋ ጻፈው በልሳነ ጽርዕ የሚልም አብነት አለ። ከአራቱ ወንጌል መጨረሻ ላይ የተጻፈ ነው[1]።