ድንት
From Wikipedia, the free encyclopedia
ደ ዱ ዲ ዳ ዴ ድ ዶ ዷ
ድንት (ወይም ድልት) በአቡጊዳ ተራ አራተኛው ፊደል ነው። እንዲሁም በከነዓን በአራማያና በዕብራይስጥ በሶርያም ፊደሎች አራተኛው ፊደል «ዳሌት» ይባላል። በዓረብኛ ደግሞ ተመሳሳይ ፊደል «ዳል» ተብሎ በ«አብጃድ» ተራ 4ኛ ነው። (በዘመናዊ ተራ ግን 8ኛው ነው።) በግሪክም 4ኛው ፊደል «ዴልታ» ይባላል። በነዚህ ቋንቋዎች ሁሉ አጠራሩ «ድ» ነው።
በአማርኛ ደግሞ «ጀ ጁ ጂ ጃ ጄ ጅ ጆ» ከ«ደ...» ትንሽ ተቀይሯል።