ጆን ሎክ
From Wikipedia, the free encyclopedia
ጆን ሎክ ( 29 ነሐሴ 1632 – 28 ጥቅምት 1704), የለዘብተኝነት (ሊብራሊዝም) አባት በመባል የሚታወቀው ሎክ የእንግሊዝ ፈላስፋና ሐኪም ነበር። [1][2][3] የሎክ ጽሑፎች በፈረንሳዊዎቹ አብዮተኞች ቮልቴር እና ሩሶ ዘንድ የሰረጸና በስኮትላንድ አሳቢዎች እና እንዲሁም በአሜሪካ አብዮተኞች ዘንድ ተሰሚነት የነበራቸው ነበሩ። በአሜሪካ የነጻነት ድንጋጌ ላይ የጆን ሎክ ስም ሰፍሮ ይገኛል። [4]
የሎክ ኅልዮቶች (ሃሳቦች) ብዙ ጊዜ የሚያጠነጥኑት በማንነት ጥያቄወችና በራስ ግምት ላይ ነበር። እንደ ሎክ አስተሳሰብ ሁሉም ያለምንም ዕውቀት እንደተወለደ የታመነ ነበር። ማናቸውም እውቀቶች የሰው ልጅ ከተወለደ በኋላ በተጨባጩ አለም ሲኖር ከሚያጋጥመው ተመክሮ የሚመነጭ ነው [5]፡፡