ሼክስፒር
From Wikipedia, the free encyclopedia
ዊሊያም ሼክስፒር (ታህሳስ ወር 1564 - ታህሳስ 23 ቀን 1616 እ.ኤ.አ.) በብዙወች ዘንድ ታላቁ የእንግሊዝኛ ጸሃፊ ተብሎ የሚገመት በእንግሊዝ አገር የኖረ ገጣሚ፣ ተውኔት ደራሲ፣ ድራማ አዘጋጅ ነበር። አብዛኛው ተውኔቶቹ ትራጄዲንና ታሪክን የተመረኮዙ ነበሩ። የኮሜዲ ጽሁፎችንም አቅርቧል። የግጥሞቹና ተውኔቶቹ አንኳር ሃሳቦች የሚያጠነጥኑት የፍቅር፣ ቅናት፣ ንዴትና መሰል ጠንካራ ስሜት ያለው ሰው ሰው ስለመሆን ናቸው። ሼክስፒር ጽሁፎቹን የመዘገባቸው በ1590 እና 1613 እ.ኤ.አ. መካከል ነበር።