ትግርኛ
From Wikipedia, the free encyclopedia
ትግርኛ በኢትዮጵያና በኤርትራ የሚነገር የሴማዊ ቋንቋዎች ቤተሰብ አባል ነው። ትግርኛ በኢትዮጵያ የብሄረ ትግራይ ( ተጋሩ ) ኣፍ መፍቻና 3ኛ ከፍተኛ የተናጋሪ ቁጥር ያለዉ ቋንቋ ሲሆን በኤርትራ ደግሞ የብሔረ ትግርኛ የአፍ መፍቻ ቋንቋ ነው:: የቋንቋው ተናጋሪዎች ከ11 ሚሊዮን በላይ ይሆናሉ ተብሎ የሚገመት ሲሆን ፣ ከዚህ ውስጥ ከ8 ሚሊዮን በላይ በትግራይና በተቀሩት የኢትዮጵያ ክፍሎች የሚነገር ሲሆን በኤርትራ ከ3 ሚሊዮን በላይ ተናጋሪዎች እንዳሉት ይገመታል:: በኤርትራ የአገሪቱ የሥራ ቋንቋና ኣብዛኞቹ የሌላ ቋንቋ ተናጋሪዎች እንደ መግባብያ የሚጠቀሙበት ቋንቋ ነው::
ትግርኛ ቋንቋ የግዕዝን ፊደል የሚጠቀም ሲሆን በ ኤርትራ አሁን ብሄረ ትግርኛ በመባል የሚታወቀው የሦስቱ አውራጃዎች ማለትም የሓማሴን: ሰራየ ና ኣከለጉዛይ ሕዝብ የሚጠቀሙበት ሕጊ-እንዳባ የተባለው የህግ ስርዓት ተጽፎበት የሚገኝ ሲሆን የመጀመርያዉ የቋንቋዉ ጽሁፍ ደግሞ ሕጊ ኣድግና ተገለባ የሚባለዉ የኣከለጉዛይ ሕገ ስርዓት ነዉ[1]።